“መሪዎች የሕዝብን ፍላጎት ማስቀደም ይኖርባቸዋል” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)

8

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር መሪዎች ጋር በወቅታዊ የሰላም፣ የጸጥታ፣ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ ነው።

በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክትል አሥተዳዳሪ ሹመት ጥላሁን የዞኑን አንጻራዊ ሰላም ለማስጠበቅ እና ማኅበረሰቡን የልማት ተሳታፊ ለማድረግ ተሠርቷል ብለዋል።

መንግሥት የክልሉን ሕዝብ መጻኢ ዕድል አቅጣጫን በማመላከት እና የውይይት መድረኮችን በመፍጠር እያከናወነ ያለው ተግባር ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) የሥራ ኀላፊዎች “ከራስ ፍላጎት በላይ የሕዝብን ፍላት ማስቀድም ይኖርባቸዋል” ብለዋል። የማኅበረሰቡን የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን የሚፈታ የጋራ አቅም እንዲኖራቸውም አሳስበዋል።

ተቋማት በሕግ እና በመርሕ፤ ክህሎት ባላቸው ሰዎች ሲመሩ የሀገረ መንግሥት ግንባታ የተሳለጠ እንደሚኾንም ጠቁመዋል።

የዋግኽምራ ብሔረሰብ የንግድ ማዕከል እና የሕዝብ የግንኙነት መንገድ ኾኖ እያገለገለ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። ዋግ በኪነ ሕንጻ፤ በሥነ ጥበብ እና በሥነ ጽሑፍ እንደሚታወቅም አንስተዋል።

የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን ከማስቀመጥ ባሻገር ዋግን ወደ አሥተሳሳሪነት ታሪኩ እና ከፍታው የሚመልሱት መሪዎችን ለመፍጠር ውይይት እናደርጋለን ነው ያሉት።

ዘገቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleማይክሮሶፍት የዊንዶውስ 10 ተጠቃሚዎች ኮምፒውተራቸውን ከጥቃት የሚከላከል ማሻሻያ አስተዋውቋል።
Next articleሕዝቡ ግጭትና ውድመትን በማውገዝ ሰላምን ተቀዳሚ አጀንዳው አድርጓል።