
ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በክልሉ በሚገኙ አየር ማረፊያዎች ለሚሠሩ ታክሲዎች የታሪፍ ማሻሻያ እንደተደረገ በተለያዩ ማኅበራዊ ገጾች እየተሠራጨ ይገኛል። አሚኮ እውነት ማጣሪያም የተሰራጨውን መረጃ ከሚመለከተው አካል አጣርቷል።
የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው የአማራ ክልል መንገድ፣ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ቢሮ ከተሰጡት ተግባር እና ኃላፊነቶች መካከል የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ጣሪያ እና ወለል በጥናት ላይ ተመስርቶ ይወስናል።
በዚህም መሠረት የኤርፖርት ታክሲዎችን አሠራር ለማዘመን መመሪያ ቁጥር 17/2018 የአየር ማረፊያ ታክሲዎች አሠራር እና አደረጃጅት መመሪያ ወጥቶ ሥራ ላይ እንደዋለ እና የሚሰሩበትን የአገልግሎት ታሪፍ ቢሮው እንደሚወስን ተቀምጧል።
ስለሆነም በክልሉ የአየር ማረፊያ ባለባቸዉ ከተሞች አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች አጠቃላይ ወጫቸዉን እና የሚጓዙትን እርቀት ታሳቢ ያደረገ ታሪፍ በከተሞች እንደተቀመጠ ነው በማኅበራዊ ገጾች እየተሠራጨ የሚገኘው።
በዚህ መሠረት፦
👉 በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ ታክሲዎች ከመሸንቲ፣ ዘጌ እና ጭስ አባይ ከተሞች ዉጭ ከከተማ ወደ አየር ማረፊያ ሲያደርሱም ኾነ ሲመልሱ አንድ ሰው ብቻውን አንድ ታክሲ ይዞ የመሄድ ፍላጎት ካለው የተሳፋሪውን ሻንጣ ጨምሮ 250 ብር ብቻ ይከፍላል፡፡ አንድ ታክሲ ሁለት እና ከዚያ በላይ የኾኑ ተሳፋሪዎችን በአንድ ላይ ይዞ የሚጓዝ ከኾነ ደግሞ የተሳፋሪዎችን ሻንጣ ጨምሮ ለእያንዳንዱ ሰው 150 ብር ብቻ ያስከፍላል፡፡
👉 ጎንደር ከተማ ለሚሠሩ ታክሲዎች ከከተማ ወደ አየር ማረፊያ ሲያደርሱም ኾነ ሲመለሱ ለአንድ ሰዉ ሻንጣን ጨምሮ 300 ብር
👉ከደሴ ኮምፖልቻ ለሚሠሩት ታክሲዎች ለአንድ ሰዉ ሻንጣን ጨምሮ 300 ብር
👉 ላሊበላ ከተማ ለአንድ ሰዉ ሻንጣን ጨምሮ 200 ብር ማስከፈል እንዳለባቸዉ ታሪፍ እንደተወሰነ እና ከመጋቢት 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉን የሚያሳይ መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ይገኛል።
በአማራ ክልል መንገድ፣ ትራንስፖርት ሎጀስቲክስ ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦት ስምሪት ዳይሬክተር ጌታቸው መርሻ
መረጃው እውነት መኾኑን እና ታክሲዎች በሚጓዙት ኪሎ ሜትር ታሳቢ ተደርጎ ማሻሻያ ማድረግ መቻሉን አሚኮ አረጋግጧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
