
ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 👉 በአጭር የጽሑፍ መልዕክት፦ አጭበርባሪዎች ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ፣ ከቢዝነስ አጋር ወይም ከመንግሥት መሥሪያ ቤት የተላከ በማስመሰል በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ያጭበረብራሉ።
👉 በስልክ ጥሪ፦ ሌላኛው የማጭበርበሪያ መንገድ በስልክ ጥሪ የሚከሰት መኾኑን መረጃዎች ያሳያሉ። አጭበርባሪዎች ጥሪዎችን ከባንክ፣ ከቴሌኮም አቅራቢዎች፣ ከሕግ አስከባሪዎች እና መሰል ተቋማት የደወሉ በማስመሰል ያታልላሉ።
👉በኢሜይል፦ ከአጭበርባሪዎች የተላኩ ኢሜይሎች እውነተኛ ይመስላሉ፤ ነገር ግን በደንብ ሲመረመሩ ገንዘብን ወይም መረጃን ለመስረቅ የተነደፉ አደገኛ ሊንኮች እና አባሪዎችን ይኾናሉ። በባሪያቸዉ አስቸኳይ የሚሉ እና ከመንግሥት ወይም ከሕግ አስከባሪ ተቋማት የተላኩ መስለዉ ይላካሉ።
👉 በማኅበራዊ ሚዲያ፦ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ለአጭበርባሪዎች የተመቹ ናቸዉ። አጭበርባሪዎች ሀሰተኛ አካዉንቶችን እና ፕሮፋይል በመለጠፍ ጓደኛ፣ ወዳጅ እና የቅርብ ሰዉ በመምሰል ያጭበረብራሉ።
👉 በድረ ገጽ፦ አጭበርባሪዎች የታወቁ ካምፓኒዎች ለመምሰል ሀሰተኛ ድረ-ገጾችን ይፈጥራሉ። ከዚህ ባሻገር ታዋቂ ሰዎችን ምስክርነት እንደሰጡ በማስመሰል ለማታለል የሚሞክሩ ናቸው።
👉 በአካል፦ አንዳንድ ማጭበርበሮች በአካል ይፈጸማሉ። ቤት ለቤት፣ እየተዝናኑ ወይም ታክሲ እየጠበቁ፣ በአደባባዮች እና በተለያዩ ቦታዎች ወደ እርስዎ ቀረብ ብለዉ ለአንድ ‘የበጎ አድራጎት ድርጅት’ መዋጮ እየሰበሰቡ በመምሰል መዋጮ ሊጠይቁ ይችላሉ።
ከዚህ ባለፈ ግላዊ መረጃዎችን ለማግኘት እንዲረዳቸዉ የዳሰሳ ጥናት እየሠሩ በማስመሰል ፎርም በማስሞላት መረጃዎችን በመመንተፍ ሊያጭበረብሩ ይችላሉ።
ስለዚህ ጥንቃቄ በማድረግ ራስን ከአጭበርባሪዎች መጠበቅ ያስፈልጋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
