ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) በሀረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ የተሠራውን የገጠር ኮሪደር ጎበኙ።

16
ባሕር ዳር: የካቲት 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) በሀረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ ውስጥ የተሠራውን የገጠር ኮሪደር ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በሀረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ ውስጥ የተሠራው የገጠር ኮሪደር ሥራ በአካባቢው በተገኙ ቁሳቁሶች፤ በኅብረተሰብ ተሳትፎ የተከናወነ የአነስተኛ መንደር ሞዴል ክንውን መኾኑን ገልጸዋል።
የአካባቢው ነዋሪ በንቃት የተሳተፈበት የገጠር ኮሪደር ሥራ ባሕላዊ የግንባታ ዘዴን፣ የተደራጀ እቅድ እና ተግባራዊ የአሠራር ውጤት ያሳየ ነው ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ መጠቀም ይገባል።
Next articleየባሕር በር የትውልድ ሕልውና ነው።