የጥንቃቄ መልዕክት፦

5
ባሕር ዳር: የካቲት 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቴሌግራም አካውንት በጠላፊዎች እንዳይወድቅ የሚደረግ ጥንቃቄ
👇
👉 ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) መጠቀም። ጠላፊዎች የኤስኤምኤስ (SMS) ኮድ ቢሰርቁ እንኳ፣ እርስዎ የፈጠሩት ተጨማሪ የይለፍ ቃል (Password) ከሌላቸው አካውንትዎን መክፈት አይችሉም። እንዴት ይተገበራል? Settings > Privacy and Security > Two-Step Verification ውስጥ በመግባት ጠንካራ የይለፍ ቃል ያስገቡ።
👉 አጠራጣሪ ሊንኮችን አይጫኑ!
“የሽልማት ባለቤት ኾነዋል”፣ “አካውንትዎ ሊዘጋ ስለኾነ በዚህ ሊንክ ያረጋግጡ” ወይም “ከቴሌግራም ዋና መሥሪያ ቤት የተላከ መልዕክት” የሚሉ ይዘቶች አብዛኛውን ጊዜ የማጭበርበሪያ ዘዴዎች ናቸው። ማንኛውንም ሊንክ ከመጫንዎ በፊት ምንጩን በትክክል ያረጋግጡ።
👉 የገቡባቸውን መሳሪያዎች ይቆጣጠሩ (Active Sessions)
አካውንትዎን በሌላ ስልክ ወይም ኮምፒውተር ላይ ተጠቅመው መውጣት (Log out) ረስተው ይሆን? ወይም ሳያውቁት ሌላ ሰው እየተጠቀመበት ይሆን?
ለመፈተሽ፦ Settings > Devices ውስጥ በመግባት የማያውቁት መሳሪያ ካለ Terminate በማድረግ በአስቸኳይ ያስወግዱ።
👉 የግላዊነት ቅንብሮችን ያስተካክሉ #Privacy-Settings
የስልክ ቁጥርዎ፣ የፕሮፋይል ምስልዎ እና የ”Last Seen” ኹኔታዎ ለማያውቁት ሰው እንዳይታይ ማድረግ፣ ከማኅበራዊ ምህንድስና ጥቃቶች ይጠብቅዎታል።
ምንጭ፦የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አሥተዳደር
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየድርማ መስኖ ፕሮጀክት አፈጻጸም ለሌሎች ፕሮጀክቶች ትምህርት የሚሰጥ ነው፡፡
Next articleምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ መጠቀም ይገባል።