ሴቶች ወደ መሪነት እየመጡ ውጤታማ እየኾኑ ነው።

13

 

ባሕር ዳር: የካቲት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በውይይት አክብሯል።

የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ ባንቺ አምላክ ገብረ ማርያም ተቋሙ ሴቶችን ለማብቃት እና ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ ነው ብለዋል።

የሴቶች ቀን መከበሩ ሴቶች ከውሳኔ ሰጭነት እስከ ፈጻሚነት ተሳታፊ እንዲኾኑ አስችሏል ነው ያሉት።

ሴቶች በሥልጠና አቅማቸውን እንዲያሳድጉ፤ በሞሰብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ለሴቶች ቅድሚያ በመስጠት ተጠቃሚ እንዲኾኑ እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።

ሴቶች ወደ መሪነት እየመጡ እና ውጤታማ እየኾኑ እንደሚገኙም አንስተዋል። ሴቶች ተቋሙን በጥንካሬ ለማገልገል እያደረጉት ያሉትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስዋል።

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች እኩል ተጠቃሚ የሚያደርጋቸውን መሪ እንዲመርጡም አስገንዝበዋል።

የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ዝና ጌታቸው ሴቶች በማኅበራዊ እና በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲኾኑ መሠራቱን ተናግረዋል።

የሕጻናት ማቆያ እና መንከባከቢያ ማዕከላትን በማቋቋም የሴቶችን ችግር ለመቅረፍ ተሠርቷል ነው ያሉት።

የአማራ ክልል የሴቶች ማኅበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር እንየ ገነቱ ሴቶች በሚሠሩበት ተቋም የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ መሠራቱን ተናግረዋል።

በመተጋገዝ፣ በመደጋገፍ እና በጥንካሬ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጋራ መሥራት እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም የሴቶች ቀን መከበሩ ሴቶች በኢኮኖሚ እና በማኅበራዊ ዘርፍ ተጠቃሚ እንድንኾን አስችሎናል ብለዋል።

በተሠማሩበት ሙያ ይበልጥ ለማገልገል እና ራሳቸውን ለማብቃት እንደሚሠሩም ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆቿ በሚከፍሉት መስዋዕትነት ጠላቶቿን እያሳፈረች ነው” ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ
Next articleእስከመቼ ነው ?