
ደሴ: የካቲት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ መሪዎች በወሎ ቀጣና በወቅታዊ ክልላዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች ዙሪያ እየተወያዩ ነው።
በውይይቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ምሥራቅ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አሰፋ ቸኮልን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ውይይቱ አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ ያተኮረ መኾኑ ተገልጿል።
በየአካባቢው አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም በመገንባት ለሌሎች ሥራዎች አስቻይ ሁኔታን መፍጠር አንደሚገባ ተነስቷል።
በውይይቱ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ተመላክቷል።
ዘጋቢ:-አሊ ይመር
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
