
ባሕር ዳር: የካቲት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወልቃይት ወረዳ “የመምረጥ እና የመመረጥ መብት ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ነው” በሚል መሪ መልዕክት የፌደሬሽን ምክር ቤት እና የምርጫ ቦርድ ውሳኔን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ሰልፈኞቹ የመምረጥና የመመረጥ መብት ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ነው፤ የፌደሬሽን ምክር ቤት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውክልና እንዲኖረን መወሰኑን እያመሰገንን በአማራ ክልል ምክር ቤት ውክልና እንዲኖረን እንጠይቃለን፤ ትግላችን ራስን የመኾን ፍትሐዊና ሕጋዊ ትግል ነው ብለዋል።
ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያችን የሕልውና ዘብ ነው፤ አማራ ነን እንጂ አማራ እንሁን አላልንም፤ እምቢ ለዳግም ባርነት፤ በደም የተከበረው አማራዊ ማንነታችን በሕግ እና በላባችን ይጸናል የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችንም አስተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
