
ባሕር ዳር፡ የካቲት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ የመምረጥ እና የመመረጥ መብትን የሚጠይቅ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፉ “የመምረጥ እና የመመረጥ መብት ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ነው” በሚል መልዕክት ነው እየተካሄደ የሚገኘው። በሰልፉ የአምስት ወረዳ ሕዝብ የተሳተፈ ነው።
በሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፉ የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ አላማጣ ከተማ፣ ኮረም ከተማ እና የኦፍላ ወረዳ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ከሰሜን ወሎ ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ እንዲሳተፍ ያስቀመጠው ውሳኔ ተግባራዊ እንዲኾን የሚደግፍ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
