
ባሕር ዳር: የካቲት 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ስፓይዌር (Spyware) የግለሰብን ጥብቅ መረጃ ግለሰቡ ሳያውቅ ለመሠብሠብ እና ለመስረቅ ታስቦ የሚዘጋጅ ግብረ-እኩይ የሶፍትዌር አይነት ነው፡፡
በመኾኑም ስልክ ያልተለመዱ ባሕሪዎች የሚያሳይ ከኾነ በስፓይዌር የተጠቃ ሊኾን ይችላል። ስለዚህ አፋጣኝ የመፍትሄ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡
👉ስልክ በስፓይዌር (Spyware) እንደተጠቃ የሚያሳዩ ምልክቶች፦
-የስልክዎ ካሜራ እና ድምጽ መቅጃ ከእርስዎ እውቅና ውጭ በርቶ መገኘት
-ጥሪ በሚያስተናግዱበት ወይም በሚደዉሉበት ወቅት ያልተለመደ ወይም የሚረብሽ ድምጽ መሰማት
-ስልክዎ ሥራዎችን የመከወን አቅሙ መቀነስ ወይም እጅግ ቀርፋፋ መኾን
-ስልክዎ በተደጋጋሚ በከፍተኛ ደረጃ መሞቅ
-ያልተለመዱ መልዕክቶችን ማስተናገድ
-ከእርስዎ እውቅና ውጪ በስልክዎ ላይ የተጫኑ መተግበሪያዎችና ፋይሎች መገኘት፤
👉የስፓይዌር ጥቃትን እንዴት መከላከል ይቻላል?
-የስልክዎን የየእለት እንቅስቃሴ በአንክሮ ይከታተሉ
-በስልክዎ የተጫኑ መተግበሪያዎችን ደህንነት እና ተዓማኒነት ማረጋገጥ ይገባል።
(Go to settings > security > trusted certificates to identify
unrecognized CA certificates often used for HTTPS interception.) በዚህ ማረጋገጥ ይገባል።
-ለተለያዩ መተግበሪያዎች የሚሰጡትን ፈቃድ በጥሞና ይመልከቱ፤ በስልክዎ ላይ የሚጭኗቸው መተግበሪያዎች የስልክዎን ካሜራ፣ የድምጽ መቅጃ፣ ጂ.ፒ.ኤስ ወ.ዘ.ተ ፈቃድ በሚጠይቁበት ጊዜ ከመፍቀድዎ በፊት በጥሞና ማጤን፤
-በስልክዎ የሚገኙ ወሳኝ መተግበሪያዎችን እና ፋይሎችን በባለሁለት ወይም በባለብዙ ደረጃ የይለፍ ቃል ይቆልፉ (Enable 2FA/MFA on critical accounts)፤
-የስልክዎን የመረጃ ማከማቻ (device storage) ይመስጥሩ፤
• ተቋማት ለሠራተኞቻቸው የሚኾን የሞባይል ደህንነት አሥተዳደርን ተግባራዊ ማድረግ (Implement Mobile Device Management (MDM) policies to limit app installations and perform regular device audits.)፤
-በስልክዎ የሚገኙ መተግበሪያዎችን እና የስልክዎን ፈርምዌር በየጊዜው ያዘምኑ (Regularly update device firmware and applications) እነዚህን ምክረ ሃሳቦች በመተግበር የስፓይዌር ጥቃትን መከላከል ይቻላል።
ምንጭ፦ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አሥተዳደር
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
