
ባሕር ዳር: የካቲት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ልዑካቸው የአዘርባጃን የሕዝብ አገልግሎት እና ማኅበራዊ ፈጠራ የመንግሥት ኤጀንሲ (ASAN) የፈጠራ ማዕከልን ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱ አዘርባጃን በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሚመራ አሥተዳደርን ለማስፋፋት እና የሕዝብ አገልግሎቶችን በዲጂታል ለማዘመን የምትከተለውን ስትራቴጂያዊ አካሄድ የሚያሳይ ነው።
በተጨማሪም በሀገሪቱ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ኢንጂነሪንግ እና የአመራር ሥልጠና ዋና ማዕከል የኾነውን የ AI አካዳሚን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ልዑኩ ጉብኝቱን በመቀጠል በክልሉ ውስጥ ካሉ ትላልቅ የነዳጅ እና የጋዝ ማቀነባበሪያ ማዕከላት አንዱ ወደኾነው ሳንጋቻል ተርሚናል እና ወደ አላት ነፃ የኢኮኖሚ ቀጣና አምርቷል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው እነዚህ ጉብኝቶች በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢነርጂ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትብብር ይበልጥ የማጠናከር አቅም አላቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
