ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

6
ባሕር ዳር: የካቲት 20/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአዘርባጃን ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ጋር ተወያይተዋል። በአዘርባጃን ባኩ ዛጉልባ ፕሬዝዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከተካሄደው ውይይት በመቀጠል፣ ሁለቱ መሪዎች በመከላከያ እና በበርካታ መስኮች በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነዶች የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።
‎ከተፈረሙ የመግባቢያ ሰነዶች መካከል 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባዔ (COP32) ማዘጋጀት፣ በግብርና፣ በሚዲያ ልማትና ልምድ ልውውጥ፣ በኢንቨስትመንት ማስፋፊያ እና በጸረ ሙስና ትብብር ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው።
‎ የአዘርባጃንን የአገልግሎት ዘርፍ ዝመናን በግንባር ቀደምትነት እየመራ የሚገኘው ተቋም “አሳን” (ASAN) እና በኢትዮጵያ የመሶብ አገልግሎት መካከል በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው እነዚህ ስምምነቶች እና የመግባቢያ ሰነዶች በሁለቱ ሀገራት መካከል ባሉ ቁልፍ ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ እና እንደሚያሰፋፉ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የደንበኞችን እርካታ 96 በመቶ ማድረስ ተችሏል።
Next articleሕዝብን ማዕከል ያደረገ የጸጥታ ሥራ መሥራት ይገባል።