የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።

20

 

ባሕር ዳር: የካቲት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ለይፋዊ ሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዝዳንቱ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ውጭ ጉዳይ ሚኒቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ጠቁሟል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጤና ሚኒስቴር በደቡብ ወሎ ዞን ሁለት ወረዳዎች መልሰው የተደራጁ የጤና ተቋማትን ርክክብ አካሄደ።
Next articleየዳንግላ-ጃዊ አስፋልት መንገድ ሥራ ለምን ተቋረጠ?