
አዲስ አበባ: የካቲት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የተቋማት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸሙን በአዳማ ከተማ ገምግሟል።
በመድረኩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ባለፉት ስድስት ወራት በመሥሪያ ቤቱ በርካታ አበረታች ውጤቶች የታዩበት መሆኑን አንስተዋል።
በግማሽ ዓመቱ በመሬት ልማት ማኔጅመንት፤ በመኖሪያ ቤት አቅርቦት፤ በከተማ መሠረተ ልማት፤ በከተሞች ምግብ ዋስትና፤ በሥራ ፈጠራ እና በሌሎች መስኮች ጠንካራ እና ውጤታማ ተግባራት መሠራታቸውን ገልጸዋል።
የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ በተሠራ ተግባር በሀገሪቱ እስካሁን በ235 ከተሞች ቁልፍ ተግባራት መከናወናቸውን አስታውቀዋል።
“የኮሪደር ልማት የብልጽግና መንግሥት እሳቤ ማሳያ ነው” ሲሉም ተናግረዋል ሚኒስትሯ።
ዘጋቢ፦ ተመስገን ዳረጎት
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
