“የሀገር መከላከያ ሠራዊት ታላላቅ ሀገራዊ ተልዕኮዎችን ይፈጽማል፤ ሕዝብ ደግሞ አካባቢውን በትጋት ይጠብቃል” አቶ ደስታ ሌዳሞ

5

 

ባሕር ዳር: የካቲት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ሌሎችም ከፍተኛ መሪዎች በመድረኩ ላይ ተገኝተዋል።

በዕለቱ መልእክት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ውጊያዎችን በአጭር ጊዜ የመጨረስ ጥበብ እና ጀግንነት ያለው መኾኑን በሚያደርጋቸው ትርኢቶች አሳይቶናል ብለዋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳር ድንበር ይጠብቃል፤ ታላቅ ሀገራዊ ተልዕኮዎችንም በብቃት ይፈጽማል፤ ሕዝቡ ደግሞ አካባቢውን በንቃት ይጠብቃል ብለዋል። ለሠራዊቱም ደጀን መኾን ያስፈልጋል ነው ያሉት።

መላው የሲዳማ ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመኾን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂው ዘርፍ የፈጠራ ችሎታ ያላቸውን ታዳጊዎች በማብቃት በኩል በትኩረት እየሠራ ነው።
Next articleለሀገር ዕድገት የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መኾኑን የደባርቅ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ።