ምርጫ ቦርድ 48 የፖለቲካ ፖርቲዎችን የመወዳደሪያ ምልክት አስተዋወቀ።

32

 

አዲስ አበባ: የካቲት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

ቦርዱ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመወዳደር የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመወዳደሪያ ምልክት እያስተዋወቀ ይገኛል። ለጠቅላላ ምርጫው ለመወዳደር የተመዘገቡ 48 የፖለቲካ ፖርቲዎችን የመወዳደሪያ ምልክት አስተዋውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ ቦርዱ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዕጩ ተወዳዳሪዎች የሚገዙበትን የሥነ ምግባር ደንብ አዘጋጅቷል። በደንቡ ዙሪያ የፊርማ መርሐ ግብርም ተካሂዷል።

የሥነ ምግባር ደንቡ ተፎካካሪ ፖርቲ አባላት እና ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንዲሁም ደጋፊዎች ሊፈጽሟቸው የሚገቡ ደንቦችን የያዘ ነው።

ደንቡ የተዘጋጀው ምርጫውን ፍትሐዊ፣ ገለልተኛ እና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ ነው ሲል የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

ዘጋቢ፦ ተመስገን ዳረጎት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየፖለቲካ ፓርቲዎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት እያደረጉ ነው።
Next articleየስጋ ደዌ በሽታ ላይ በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል።