
ወልድያ፡ የካቲት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ተአማኒ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲኾን እየሠሩ መኾናቸውን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር እና የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኀላፊዎች ተናግረዋል።
የሥራ ኀላፊዎቹ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት አስመልክቶ ከአሚኮ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ከድር ሙስጠፋ የምርጫ ሂደቱ ዴሞክራሲያዊ እንዲኾን በየደረጃው ላሉ የፓርቲው አባላት ሥልጠና እየተሰጠ መኾኑን ገልጸዋል።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋዬ ገብሬ መንግሥት ኀላፊነት ወስዶ የጸጥታ ችግር ያለባቸውን ቀበሌዎች ሰላም የማጽናት ሥራ እየሠራ ነው ብለዋል።
የፌዴራል እና የክልል ምክር ቤት እጩ አባላትን አዘጋጅተው ማጠናቀቃቸውንም የሥራ ኀላፊዎቹ ለአሚኮ ገልጸዋል።
የጸጥታ ችግር የምርጫ ሂደት ስጋት መኾኑን እንደገመገሙ የተናገሩት ኀላፊዎቹ መንግሥት ሕግ የማስከበር ሥራውን ይቀጥላል ብለዋል።
የመራጩን ሕዝብ እና የምርጫ አሥፈፃሚዎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አንስተዋል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዕድገት ያስመዘገበችበት፣ ገጽታዋ የተቀየረበት፣ ትልልቅ ፕሮጀክቶች እያስመረቀች እና አዳዲስ እየገነባች ያለችበት ወቅት ላይ መካሄዱ የተለየ እንደሚያደርገውም አስረድተዋል።
ዕድሜው ለምርጫ የደረሰ ሁሉ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ ይበጀኛል፣ ይመራኛል የሚለውን ፓርቲ መርጦ መንግሥት የመመስረት ዕድሉን በአግባቡ እንዲጠቀም ምርጫ ቦርድ ባወጣው መርሐ ግብር ተመዝግቦ ካርዱን እንዲይዝ አስገንዝበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
