ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሶርጋ ኢኮ ሎጅን ጎበኙ።

18

 

ባሕር ዳር: የካቲት 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሶርጋ ኢኮ ሎጅን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ‎በሶርጋ ሐይቅ ላይ የሚገኘው የሶርጋ ኢኮ ሎጅ በአሁኑ ወቅት በ14 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የፕሮጀክቱ ሥራ በፍጥነት እየተከናወነ ነው፤ በቅርቡ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት። ከነቀምቴ ከተማ በ6 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ብቻ የሚገኘው የሶርጋ ኢኮ ሎጅ አካባቢውን ከመጠበቅ ባሻገር በኮንስትራክሽን እና በተለያዩ አገልግሎቶች የሥራ እድል እንዲፈጥር ተደርጎ የተቀረጸ መኾኑን አንስተዋል።

ፕሮጀክቱ የአካባቢውን ማኅበረሰብ በመጥቀም በክልሉ ዘላቂ ቱሪዝምን የሚያበረታታ ይኾናል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢንዱስትሪዎችን የኃይል አቅርቦት ለማሻሻል እየተሠራ ነው።
Next articleበአማራ ክልል ከ319 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ስንዴ እየለማ ነው።