
ባሕር ዳር: የካቲት 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የጎኖፋ የተቀናጀ የምግብ ኢንዱስትሪ ግንባታን አስምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ያስጀመርነው የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ የተቀናጀ የምግብ ኢንዱስትሪ ግንባታ የበቆሎ፣ ማሽላ ዱቄት እና 14 ተጓዳኝ የበቆሎ ውጤት ምርቶችን ለማምረት የታቀደ ነው ብለዋል።
ፕሮጀክቱ ተጠናቅቆ ወደ ሥራ ሲግባ በቀን 2000 ቶን በቆሎ እና 120 ቶን ማሽላ የማምረት አቅም ይኖረዋል ነው ያሉት። ከ6 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ሠራተኞች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ እድል የሚፈጥር ነው። ለአካባቢው አርሶአደሮች፣ ለኅብረት ሥራ ማኅበራት እና የግል ዘርፍ አምራቾች የእሴት ሰንሰለትን በማገዝ ለአካባቢው አርሶአደሮች ሰፊ ገበያ ይፈጥራል፣ የአካባቢውን ኢኮኖሚ ያሳድጋል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
