
ዛሬ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጋር የነቀምቴ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተናል።
ይህ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ በኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣ በ250 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ የሚገኝ ነው።
ፓርኩ በአካባቢው ለሚገኙ፣ በተለይም በአራቱ የወለጋ ዞኖች ለሚገኙ ገበሬዎች ታላቅ የገበያ ዕድል የፈጠረ ነው። የገበሬዎችን ምርት ይረከባል፤ ያቀነባብራል፤ እንዲሁም ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ያቀርባል።
በግብርና የጀመርነው እመርታ በአግሮ ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች ካልተደገፈ ውጤታማ አይሆንም። በዚህ ረገድ በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው ተግባር የግብርና ዕድገታችንን የሚያሣልጥ ነው።
