“አርሶ አደሮቻችን እያመረቱ ብቻ አይደለም፤ ከመዋጮዎቻቸውም እሴት እያፈሩ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

6

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት አርሶ አደሮቻችን እያመረቱ ብቻ አይደለም፤ ከመዋጮዎቻቸውም እሴት እያፈሩ ይገኛሉ ብለዋል።

በ1996 ዓ.ም የተመሠረተው የጊቤ ዲዴሳ የገበሬዎች የኅብረት ሥራ ማኅበር 207 የመጀመሪያ ደረጃ ማኅበራትን ያቀፈ ነው።

167 ሺህ ገበሬዎችን የሚያገለግለው ማኅበሩ አሁን ላይ የግብርና ግብዓቶችን ከማቅረብ ተሻግሮ የምርት እሴትን ወደመጨመር አሳድጓል። ማኅበሩ በቅርቡ ዘመናዊ የእህል ወፍጮ ያቋቋመ ሲሆን በቀን 1200 ኩንታል የበቆሎ ዱቄት የማምረት አቅም አለው። በ2.8 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባው ፋብሪካ ለአካባቢው ጊዜያዊ እና ቋሚ የሥራ እድሎችን ፈጥሯል።

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የአርጆ ድንጋይ መፍጫ ፋብሪካን ጎበኙ።
Next articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልእክት፦