
ባሕር ዳር: የካቲት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን ሃዋ ገላን ወረዳ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ በቄለም ወለጋ ዞን ሃዋ ገላን ወረዳ በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር የለማ የሙዝ እርሻ ከባቢን ጎብኝቻለሁ ብለዋል።
አርሶአደሮች በፍጹም ጽናት፣ ቅንጅት እና ትብብር አካባቢያቸውን በቀየረ ሥራ በመመልከቴ ደስ ብሎኛል ነው ያሉት። የተመለከትነው የእርሻ ሥራ፤ የአካባቢ መሬትን እና የውኃ ሃብትን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ መኾኑን ገልጸዋል።
ባሕላዊ የመስኖ ዘዴዎችን በመጠቀም እና በቅርብ ያለ ሃብትን በሚገባ ጥቅም ላይ በማዋል ማኅበረሰቡ ውጤታማ እና ተስፋ ሰጪ የግብርና ማዕከል መፍጠር ችሏል ነው ያሉት።
በተለይም የመንገድ መሠረተ ልማት የአርሶአደሮችን ምርት በቀላሉ ወደ ገበያ ለማድረስ የፈጠረውን እድል መመልከት እጅግ የሚያበረታታ መኾኑን ገልጸዋል።
ይኽ እድገት የልማት ጥረቶች ከአካባቢው ማኅበረሰብ ፍላጎት እና አቅም ጋር በቅርበት ሲናበቡ ሊገኝ የሚችለውን ውጤት በግልጽ የሚያሳይ ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
