
ባሕርዳር፡ የካቲት 10/2018ዓ.ም (አሚኮ) የቱርክዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ለሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባ ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር),በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ወደ ምድረ ቀደምቷ ሀገር ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።
ይፋዊ የስራ የጉብኝት ልውውጣችን በቱርክዬ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጥልቅ የአጋርነት ጥንካሬ የሚያንጸባርቅ ነው።
ከአንካራ እስከ አዲስ አበባ፤ በሁለቱ ጥንታዊ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክሩ እና ዘላቂ ትስስርን የሚያረጋግጡ ውጤታማ ውይይቶች እንዲኖሩን እመኛለሁ ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
