
ባሕርዳር ፡ የካቲት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በሁለተኛው ቀን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን፤ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
