“ሴቶችን በየዘርፉ ማሳተፍ ሀገርን በሙሉ እንደ ማሳተፍ ይቆጠራል” ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው

11
ባሕርዳር ፡ የካቲት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ30ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ተቋም ጉባኤ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት 30ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ተቋም ጉባኤ መሪ መልዕክት “የአፍሪካን ሴቶች ፈተናዎችን የመቋቋም ዐቅም መገንባት የአየር ንብረት፣ግጭቶች እና ዘላቂ ነገ” የሚል እንደመኾኑ የመሪ መልዕክቱ ዓላማ በጾታ እኩልነት፣ በጤና እና በትምህርት መርሐ ግብሮች፣ በኢኮኖሚው ዘርፍ እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የአፍሪካ ሴቶችን ዐቅም የበለጠ ማሳደግ ጠቃሚ ሚና አለው ብለዋል።
በተለይ ደግሞ ሴቶችን ማዕከል ያደረጉ የማኅበራዊ ልማት ተግባራት የሴቶችን ዐቅም የበለጠ እንደሚያጎለብቱ ገልጸዋል።
ይሄንን ታሳቢ በማድረግ በጽሕፈት ቤታችን
ባለፉት ስድስት ዓመታት 37 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤቶችን በተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት የሴቶችን እና የሕጻናትን የትምህርት ተደራሽነት ከፍ ለማድረግ ሠርተናል ነው ያሉት።
ለሴቶች የሞያና የንግድ ክሂሎት ሥልጠና፣ የመሥሪያ ቦታ፣ ግብአትና የመነሻ ካፒታል በማመቻቸት ሴቶች በገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ ተሠማርተው የራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ሕይወት እንዲቀይሩ አድርገናል ብለዋል።
ሴቶችን በየዘርፉ ማሳተፍም ሀገርን በሙሉ እንደ ማሳተፍ ይቆጠራል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ሊሳካ የቻለው ብዙ ሚሊዮን ሴቶች በፈቃደኝነት ስለተሳተፉበት ነው ብለዋል።
የአየር ንብረት መዛባትን ለመቋቋምም ኾነ ሌሎችንም የአፍሪካ ችግሮች ለመቅረፍ፤ ሴቶች ወሳኙን ቦታ የሚያገኙበትን ዐውድ መፍጠር አለብን ነው ያሉት። ለዚህ ደግሞ እኛ ቀዳማዊ እመቤቶች ከፍ ያለ ኃላፊነት አለብን ብለዋል በመልዕክታቸው።
አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) ከናሚቢያ ፕሬዝዳንት ኔቱምቦ ናንዲ ንዴትዋ ጋር ተወያዩ።
Next articleየባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የኢንቨስትመንት ማነቆዎችን ለመፍታት እየሠራ ነው።