
ባሕር ዳር: የካቲት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከ48ኛው መደበኛ የአፍሪካ ንብረት ሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ አባል የኾነችበት የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት ስብሰባ ተካሂዷል።
የምክር ቤቱ የአባል ሀገራት በዋናነት በወቅታዊ የአህጉሪቱ ሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ በተለይም ሶማሊያ እና ሱዳን ዙሪያ መክረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር) በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር በሶማሊያ አሸባሪው አል ሻባብ ሰላም እና ጸጥታ ማወኩን አሁንም እንደቀጠለ መኾኑን ገልጸዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ ለማስፈን ኢትዮጵያ እና ሌሎች ሀገራት ከፍተኛ መስዋዕትነት መክፈላቸውን አስታውሰዋል።
በዚህ ጥረት የተገኙ ሰላም እና መረጋጋት እንዳይቀለበስ በሽብር ቡድኑ ላይ የሚካሄደውን ዘመቻ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በሱዳን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ሁሉንም ሱዳናውያን አካታች የኾነ የመፍትሔ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
