የመራጮች ምዝገባ የካቲት 28 እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

6
ባሕር ዳር: የካቲት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ ምርጫ ሥራዎች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ቦርዱ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ያከናዎናቸውን ሥራዎችንም አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርጅ ዋና ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ እንዳሉት ቦርዱ የምርጫ ክልል መስፈርቱን ያሟሉ አስፈጻሚዎችን መዝግቦ እና ገለልተኝነታቸውን በማረጋገጥ ቅጥር ማከናወኑን ገልጸዋል።
የምርጫ ክልል አስፈጻሚዎች እንዴት መሥራት እንዳለባቸው አስፈላጊውን ሥልጠና ተሰጥቷል። የምርጫ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መክፈት ተችሏል ብለዋል።
የምርጫ ክልል የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላትን የማስመረጥ እና የተመረጡ ኮሚቴዎችን ደግሞ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የማሳወቅ ሥራ እየተሠራ ይገኛል ነው ያሉት።
ከምርጫ ክልል አሥፈጻሚዎች ጎን ለጎን የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎችን ብቃት በማረጋገጥ ቅጥር መፈጸሙን አንስተዋል። ስም ዝርዝራቸውንም ለፖለቲካ ፓርቲዎች ማሳወቅ መቻሉን ገልጸዋል።
ልዩ ጣቢያ ማቋቋም በሚያስፈልጋቸው እንደ የተፈናቃይ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ቦርዱ መረጃ ሰብስቧል።
በመግለጫው የተነሳው ጉዳይ የመራጮች ምዝገባ መራዘም ነው። ሰብሳቢዋ እንዳሉት የመራጮች ምዝገባ
በምርጫ ጊዜ ሰሌዳው መሠረት ከየካቲት 7/2018 እስከ መጋቢት 7/2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ መርሐ ግብር መውጣቱ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የታቀዱ ሥራዎችን ማከናወን ባለመቻሉ ምዝገባው የካቲት 28/2018 ዓ.ም እንዲጀመር ቦርዱ መወሰኑን ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ዳግማዊ ተሠራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleየአውሮፓ ኅብረት በቲክቶክ ላይ ጥያቄ አነሳ።
Next articleባለፉት ስድስት ወራት 34 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶችን መሳቡን የሰሜን ሸዋ ዞን አስታወቀ፡፡