የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለመኾን ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ቋሚ ምስክር ነው።

10
ባሕር ዳር: ጥር 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ)በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የገበታ ለትውልድ ውጥን የተገነባው እና በ13 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምግብ ቤቶችን፣ የመዋኛ ገንዳዎችን፣ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገዶችን እና የሄሊኮፕተር ማረፊያን ጨምሮ ሁሉንም ዓይነት መገልገያዎች አሟልቶ ይዟል።
በተጨማሪም በተለያዩ የፍራፍሬ ዞኖች እና ለዓይን በሚማርኩ አረንጓዴ ስፍራዎች የታጀበ በመኾኑ፤ ለጎብኚዎች የማይረሳ ትውስታን የሚሰጥ እጅግ ማራኪ ቦታ ነው።
‎ይህ ሪዞርት ከያዛቸው ዘመናዊ መገልገያዎች ባሻገር፤ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለመኾን ያላትን ቁርጠኝነት እና ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ቋሚ ምስክር ነው።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የቱሪዝም ልማቱን ከተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ፣ ከዘላቂነት እና ከአካታችነት ጋር በማቀናጀት፤ ሪዞርቱ የወሎ ሕዝብ ያለውን ጥልቅ ባሕላዊና ተፈጥሯዊ እሴት ለዓለም ማኅበረሰብ የሚያስተዋውቅበት ሰፊ ገበታ ኾኖ ያገለግላል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ባለፉት ስድስት ወራት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሠብሥቧል።
Next articleወሎን የገለጠው የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት