
ባሕር ዳር: ጥር 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሌማት ትሩፋት መንግሥት ለዜጋ እና ለሀገር ያለውን ክብር ያሳየበት ልዩ እሳቤ እና ትግበራ ነው፡ ብለዋል።
መንግሥት በሌማት ትሩፋት ዘላቂ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ፖሊሲ ትግበራ ተደማሪ አቅም በማድረግ መሥራቱንም ገልጸዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የምዕናብ ልህቀት ፈልቆ የተጀመረው ኢኒሼቲቭ የብዙ ቤተሰብን ሕይወት ቀይሯል፣ ደግሞም ወደፊትም መቀየሩን ይቀጥላል ነው ያሉት።
የሌማት ትሩፋት ለዘመናት ጸጋ ሆነው ያልታዩ ጓሮዎችን የልማት ከባቢ አድርጓል፡፡ በመኾኑም የተመጣጠነ ምግብ በሽታ መከላከልን ካስቀደመው የጤና ፖሊሲያችን ጋር ግንኙነቱ ቀጥተኛ ነው፡፡ በዚህም የመደመር እሳቤ ባፈለቀው የፈጠራ ተግባር የእንስሳት ተዋጽኦ በአግባቡ ወደ ሌማታችን አምጥቷል ብለዋል።
የሌማት ትሩፋት የተሳሰረው ከከበረ የሰዎች ከሕይወት፣ ጤና፣ ከትልቁ የሀገር መልክ እና ክብር ብሎም ከዘላቂ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ርዕያችን ጋር ነው።
በትጋት የሚሰሩ ክንዶች ሌማታቸውን አትረፍርፈዋል፤ ወደፊትም ያትረፈርፋሉ ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
