“የእናቶችን ሃዘን ማስቆም የምንችለው ችግሮችን በምክክር መፍታት ስንችል ነው” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

6
አዲስ አበባ: ጥር 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ እና ከመንግሥት ጋር ስምምነት ከፈፀሙ ታጣቂዎች አጀንጃ እያሰባሰበ ነው።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሸነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ታጥቀው ሲንቀሳቀኑ ከቆዩ አካላት ጋር በተደረገ ውይይት ላይ ባስተላለፉት መልእክት ኮሚሽኑ የተቋቋመበትን ዋና አላማ አስረድተዋል።
ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ባለፉት 50 ዓመታት በኢትዮጵያ የተካሄዱ የእርስ በእርስ ጦርነቶች ለኢትዮጵያውያን እልቂት ምክንያት እንደነበሩ አንስተው በዚህም ኢትዮጵያውያን እናቶች መርዶ እና ሃዘን ሲያስተናግዱ መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ይህን ለቅሶ እና የእናቶችን ሃዘን ማስቆም የምንችለው ችግሮችን በምክክር መፍታት ስንችል ነው ብለዋል። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንም በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀሱ ከቆዩ ወገኖች መረጃ እያሰባሰበ ነው።
ዘጋቢ፦ ተመስገን ዳረጎት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየቴክኖሎጅ ልማት ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።
Next articleየወርቅ ምርትን ለማሳደግ በተከናወነ የተቀናጀ ሥራ ውጤት መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።