የራያ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ የሕልውና ጉዳይ ነው።

26

 

ባሕር ዳር: ጥር 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ የሕወሃትን ትንኮሳ የሚቃወም ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

ሰልፈኞቹ ሕወሃት በራያ፣ በወፍላ እና ኮረም ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ወረራ አውገዘዋል። የሕውሃት ዳግም ወረራ እና ጦርነት ሊበቃ እንደሚገባም አንስተዋል።

የራያ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ የሕልውና ጥያቄ መኾኑንም ገልጸዋል። ሰልፈኞቹ እምቢ ለዳግም ባርነት አንገዛም ብለዋል። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋሉ ነው ያሉት።

ከቆቦ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚመላክተው የራያ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በሕጋዊ መንገድ እንዲፈታም ጠይቀዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያን ማንም ከመንገዷ አስቁሟት አያውቅም፤ ማንም ሊያስቆማትም አይችልም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር)
Next article“በሰላም እጦት ምክንያት ትምህርት ያቋረጡ ተማሪዎች ጉዳይ ለሀገር አደገኛ ስብራት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)