
ባሕር ዳር: ጥር 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የተለያዩ አካባቢዎቾ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በዞኑ በሚገኙ በአራቱም ወረዳዎች እና በአምስቱም ከተማ አስተዳደሮች የሕውሀትን ዳግም ወረራ እና ጦርነት በመቃዎም ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
“ከትግራይ ሕዝብ ጋር ትናንትም ዛሬም ነገም ግጭት የለንም” የሚል መልዕክት የያዙት ሰልፈኞቹ የጥፋት ኃይሉ እኩይ ሴራ ግን በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ የትግራይ ሪፐብሊክን መገንባት ነው ብለዋል።
ሰልፈኞቹ ለዳግም “እምቢ ለዳግም ባርነት” በሚል መሪ ሃሳብ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል የሚሉ ሀገራዊ ድምጾችን እያስተጋቡ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
