
ባሕር ዳር: ጥር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የዩናይትድ ኪንግደም የኮመንዌልዝ፣ ልማት ጉዳዮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቬት ኩፐርን አግኝቼ በቁልፍ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል።
ከውይይታችን ጎን ለጎን በተካሄደው የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ማዕቀፍ ሥር የኢንቨስትመንት እና ሃብት አሥተዳደር የቴክኒካል ትብብር የመግባቢያ ሥምምነት እና የሁለት የጋራ የልማት ስምምነቶች ፊርማ መርሐ ግብር ላይም ተገኝተናል ነው ያሉት።
እነዚህም የሁርሶ-አይሻ 400 ኪሎ ቮልት እና የደገሃቡር-ቀብሪደሃር 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶች ስምምነቶች ናቸው። እነዚህ ስምምነቶች ትብብርን በማጠናከር እና ስትራቴጂያዊ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ ርምጃን የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል በመልዕክታቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
