“የሸበሌ ሪዞርት የምሥራቅ ኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ትልቅ አቅም ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

10
ባሕር ዳር: ጥር 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያ ዛሬ የተስፋ ብቻ ሳይሆን የሥራ እና የተጨባጭ ውጤት ምድር እየሆነች ነው ብለዋል።
ከ’ገበታ ለትውልድ’ ዐቢይ ፕሮጀክቶች መካከል ሁለተኛው እና በ385 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የሸበሌ ሪዞርት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መኾኑን ገልጸዋል።
ሪዞርቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በተያዘው ጉዞ ላይ ትልቅ እጥፋትን የሚፈጥር መኾኑንም አንስተዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሀሳብ ዘር እስከሚታይ ውጤት በሚመነዘሩ የትጋት ልኬቶች የተጀመሩት የ“ገበታ” ፕሮጀክቶች፣ የሀገራችንን እምቅ ፀጋዎች ለዓለም ገበያ እያወጡ ይገኛሉ ነው ያሉት።
በመደመር እሳቤ እየተገነቡ የሚገኙት እነዚህ ፕሮጀክቶች ያለንን አቅም በማቀናጀት፣ ለላቀ ውጤትና ከፍታ እንድንጓዝ የሚያግዙ ናቸው ብለዋል።
የሸበሌ ሪዞርት የሶማሌ ክልልን የሀገራዊ ልማት ኢኒሼቲቭ ትሩፋቶች ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ፣ የምሥራቅ ኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ትልቅ አቅም ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleተቋርጦ የቆየው የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጄክት በቀጣይ አንድ ወር ውስጥ ወደ ግንባታ ይመለሳል።
Next articleወራሪው ጣሊያን ጦር ዶጋሊ ላይ መሸነፍ