
ባሕር ዳር፡ ጥር 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአገው ፈረሰኞች 86ኛ ዓመት ክብረ በዓል ዋዜማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው። የመርሐ ግብሩ አንድ አካል የኾነው ሲምፖዚዬምም እየተካሄደ ይገኛል።
በሲምፖዚየሙ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) እና ሌሎችም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ሲምፖዚዬሙ በአገው ፈረስ ባሕል እና በሀገረሰባዊ ጥበባት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
