
ባሕርዳር፡ ጥር 22/2018ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የኢትዮጵያ የስንዴ ፕሮግራም ምርታማነትን በመጨመር፣ የመስኖ ሥርዓትን በማስፋት፣ የዘር አቅርቦት ሥርዓትን በማጠናከር እና በዋና ዋና አካባቢዎች አነስተኛ አርሶ አደሮችን በመደገፍ የሀገራችንን ራስን የመቻል ጉዞ ግብ ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋል።
በ2018 የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሩብ ዓመታት አጠቃላይ የስንዴ ምርት 126 ነጥብ 69 ሚሊዮን ኩንታል ደርሷል። ይኽም የመስኖ ስንዴ ምርትን ሳይጨምር ነው ብለዋል።
አርሶ አደሮቻችንን ማድነቅ እና ማመስገን እፈልጋለሁ፤ ይኽንኑ የሥራ ጽናት ቀጥሉበት ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
