በአማራ ክልል መንግሥት እና አፋሕድ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ታጣቂዎች እየገቡ ነው።

28
ባሕርዳር፡ ጥር 22/2018ዓ.ም (አሚኮ)በአማራ ክልል መንግሥት እና አፋሕድ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ በትጥቅ ትግል የነበሩ ታጣቂዎች ለሰላም ገብተዋል።
ስምምነቱን ተከትሎ በሰላም የገቡት ታጣቂዎች በእብናት ወረዳ እና በአካባቢው በተለያዩ አደረጃጀቶች ታጥቀው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ናቸው።
የእብናት ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ቻላቸው መሳፍንት በተደረሰው ስምምነት የሰላምን ዋጋ ተረድታችሁ በመግባታችሁ ለሕዝባችሁ ታላቅ እፎይታ ነው ብለዋል። ሰላም ያሸንፋል፤ እንኳን በሰላም መጣችሁ ነው ያሉት።
ወንድምን ከወንድሙ በማገዳደል ክልሉ እንዲዳከም የሚሠሩ ኀይሎችን አሸንፋችሁ በመመለሳችሁ እናንተ የሰላም አርበኞች ናችሁ ብለዋል።
የእብናት ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አለበል ጌጤ ስለ ሰላም ላደረጋችሁት ቁርጠኝነት እናመሰግናችኋለን ነው ያሉት።
ከእብናት ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሌሎች በጫካ የቀሩ ወንድሞችም በሰላም ስምምነቱ መሠረት ለሰላም እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleከ193 ሚሊየን ብር በላይ ብድር ለደንበኞች ማበደሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት አስታወቀ።
Next articleእንግዶችን ለማስተናገድ ሆቴሎች በቂ ዝግጅት አድርገዋል።