
ባሕር ዳር: ጥር 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዓመታዊው የአስተርዕዮ ማርያም በዓል በጥንታዊታ ደብረ ማርያም ገዳም ተከብሯል።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በ”ጥርን በባሕር ዳር” መርሐ ግብር አካል የኾነው የአስተርዕዮ ማርያምን በዓል በጣና ሐይቅ ደብረ ማርያም ገዳም አክብሯል።
በበዓሉ መልዕክት ያስተላለፉት የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ጋሻው ገዳሙ ቀደምት እና ትልቅ ታሪክ ያለው መኾኑን ገልጸዋል።
ይህንን ሃይማኖታዊ ስፍራ በማስተዋወቅ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑንም ኀላፊው ጠቅሰዋል። ገዳሙ በጥንታዊ የአሠራር ጥበብ መጠገኑንም አድንቀዋል።
ዓባይ ከጣና በሚወጣበት ቦታ ላይ በሚገኘው ገዳም ላይ የአስተርዕዮን በዓል ማክበር ልዩ ደስታ እንደሚፈጥርም ተናግረዋል።
የገዳሙን ታሪክ እና የተፈጥሮ አቀማመጥ እንዲሁም መንፈሳዊ በረከት ለማግኘት ጎብኝዎች ደብረ ማርያም ገዳምን እንዲጎበኙም ጋብዘዋል።
በዓሉ በርካታ ምዕመናን እና የሃይማኖቱ ተከታዮች በተገኙበት በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ተከብሯል።
ዘጋቢ፦ ዋሴ ባዬ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
