“የደንበኞች ሳምንት ባንኩ ሲሰጥ የቆየውን አገልግሎት የበለጠ ለማቀላጠፍ እና ውጤታማ ሥራ ለመሥራት የሚያስችል ነው” አቶ አህመድ ሽዴ

33

 

አዲስ አበባ፡ ጥር 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ‎‎የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞች አገልግሎት ሳምንት የመክፈቻ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት እያካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደንበኞች ያሉት አንጋፋ ተቋም ነው።

የደንበኞች አገልግሎት ሳምንት መከበሩ ባንኩ ያሉትን ደንበኞች የበለጠ ለማገልገል የሚያግዝ መኾኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ኤፍሬም መኩሪያ ተናግረዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም ንግድ ባንክ ባዘጋጀው የአምሥት ዓመት ተቋማዊ ስትራቴጅ የደንበኞችን ፍላጎት ማርካት ቀዳሚ አጀንዳ መኾኑን አስታውቀዋል።

የባንኩ ሠራተኞች ደንበኞችን በማገልገል ያሳኩትን ውጤት የበለጠ ማጠናከር እንዳለባቸውም ምክትል ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።

ደንበኞችን በአገልግሎት አሰጣጥ ማርካት፣ በቅንጅት መሥራት፣ የሥራ ባሕልን የበለጠ ማጠናከር፣ የኔት ወርክ መቆራረጥን በማስወገድ እና ደንበኞችን በማገልገል የበለጠ የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ በፋይናንስ ዘርፉ የተሻለ ለውጥ እንዲመዘገብ ማድረጉን ገልጸዋል።

የደንበኞች ሳምንት ባንኩ ሲሰጥ የቆየውን አገልግሎት የበለጠ ለማቀላጠፍ እና ውጤታማ ሥራ ለመሥራት የሚያስችል ስለመኾኑም ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ተመስገን ዳረጎት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለ

Previous articleየእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፉ የሀገርን ኢኮኖሚ ከመቀየር አኳያ ያለው ድርሻ ከፍተኛ ነው።
Next articleየሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰላም አማራጭን ባልተቀበሉ ኃይሎች ላይ የተቀናጀ ርምጃ ወሰደ።