የዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ተሳታፊ እንግዶች የባሕር ዳር ከተማን የልማት ሥራዎች ጎበኙ።

14

የዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ተሳታፊ እንግዶች የባሕር ዳር ከተማን የልማት ሥራዎች ጎበኙ።

ባሕር ዳር፡ ጥር 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “የሕግ የበላይነት እና አማራጭ ያለመግባባት መፍቻ ሥርዓቶች ለዘላቂ ሰላም እና ልማት” በሚል መልእክት በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትብብር በባሕር ዳር ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ለመሳተፍ የመጡ የውጭ ሀገር ዜጎች እና ሌሎችም ተሳታፊዎች የከተማዋን የልማት ሥራዎች ጎብኝተዋል።

እንግዶች የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም፣ አዲሱ የዓባይ ድልድይ፣ የባሕር ዳር ሞሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ አዲሱ ፕላዛ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ነው ተዘዋውረው የተመለከቱት።

የውጭ ሀገር የኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የከተማዋን የልማት ሥራዎች አድንቀዋል። በተለይም በከተማዋ በምሽት ለእግር ጉዞ የተመቸች፣ አየሯ ተስማሚ ሰላሟ የተጠበቀ፣ ለኑሮ እና ለጉብኝትም የምትመች መኾኗን እንግዶቹ መናገራቸውን ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል የግብርና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ጥራት ያለው ዘር ለማቅረብ እየሠራ ነው።
Next articleየጊፋታ በዓል በዩኒስኮ መመዝገቡን ተከትሎ ዜጎች አደባባይ በመውጣት ደስታቸውን ገለጹ።