ኢትዮጵያ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረች።

18
አዲስ አበባ: ጥር 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መከሰቱን የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመኾን ኅዳር 03/2018 ዓ.ም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠር እና የኅብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በየደረጃው ከሚገኙ ተቋማት ጋር በጋራ በመኾን ድንገተኛ የኅብረተሰብ ጤና ክስተት ፈጣን ምላሽ ዕቅድ በማውጣት ሢሠራ ቆይቷል።
ቫይረሱ እንደተከሰተ የጤና ሚኒስቴር ሁሉን አቀፍ ፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድን ወደ ቦታው በመላክ የማርበርግ በሽታ ቅኝት እና ምላሽ ሥራዎችን ሲያከናውንም ነው የቆየው።
ይህ በመኾኑም አሁን ላይ የማርበርግ ቫይረስ ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ መጥፋቱን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይፋ አድርጓል።
ዘጋቢ፦ ረሕመት አደም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 79 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ።
Next articleየተደረገውን የሰላም ስምምነት የተቀበሉ የአፋሕድ መሪዎች እና አባላት በጎንደር ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።