ከግጭት ወጥቶ ጊዜን ለልማት ማዋል እንደሚገባ የአፋሕድ መሪዎች ተናገሩ።

74
አዲስ አበባ፡ ጥር 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ)
የአፋሕድ ከፍተኛ መሪዎች ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ እና ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባውን ጨምሮ የድርጅቱ ሌሎች ከፍተኛ መሪዎች በመዲናዋ ያለውን የልማት እንቅስቃሴ ተዘዋውረው እየጎበኙ ነው።
መሪዎቹ በከተማዋ የተሠሩ የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ነው የጎበኙት፡፡
በአዲስ አበባ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የልማት ሥራዎች እጅግ የሚደነቁ መኾናቸውንም ገልጸዋል።
የአፋሕድ መሪዎች እየተሠራ ያለው ሥራ ስንሰማው ከነበረው የሚቃረን ኾኖ አግኝተነዋል ብለዋል።
ሰላም የልማት ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እጅጉን አስፈላጊ መኾኑንም ነው ያስገነዘቡት። ከግጭት ወጥቶ ጊዜን ለልማት ማዋል እንደሚገባም ገልጸዋል።
ባለፉት ሦሥት ዓመታት የነበረውን የሰላም እጦት ልማት ላይ አውለነው ቢኾን ኖሮ የበለጠ ልማት ማከናዎን ይቻል ነበር ሲሉም ቁጭታቸውን ገልጸዋል፡፡
በአማራ ክልል መንግሥት እና በአፋሕድ መካከል የተደረሰውን ዘላቂ የሰላም ስምምነት ውጤታማ የሚያደርግ ስምምነት መሪዎቹ መፈረማቸው ይታወቃል፡፡
ዘጋቢ፦ ኢብራሒም ሙሐመድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleየፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
Next articleበክልሉ መንግሥት እና አፋሕድ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በታች ጋይንት ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ሰላም ገቡ።