
ባሕር ዳር፡ ጥር 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት “ጤናማ ፉክክር፣ ውጤታማ ትብብር፣ ገንቢ ምክክር፣ ለሀገር ክብር” በሚል መሪ መልዕክት ውይይት እያደረገ ነው፡፡
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ጊዜው ታከለ በባሕር ዳር ከተማ የሚንቀሳቀሱ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ላይ የተመዘገቡ የተለያዩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።
በመጭው ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ከሚወዳደሩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ብልጽግና፣ ኢዜማ፣ መኢአድ፣ አብን፣ አዴሃን፣ እናት፣ ኢሃፖ፣ ነጻነት እና እኩልነት (ነእፓ)፣ ግዮናዊ፣ አንዲት ኢትዮጵያ ባሕር ዳር ከተማ ላይ ይወዳደራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አንስተዋል። በዛሬው ምክክር ከእያንዳንዱ ተፎካካሪ ፓርቲ አምስት፣ አምስት ተወካዮች እየተሳተፋ እንደሚገኙም አንስተዋል።
ምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲከናወን ደግሞ በከተማዋ እንዴት እንሥራ በሚል ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መኾኑን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
