የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የከተራ እና የጥምቀት በዓል በድምቀት እንዲከበር ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረበ።

6

 

ባሕር ዳር: ጥር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የከተራ እና የጥምቀት በዓል በደመቀ እና ባማረ መልኩ እንዲከበር አስተዋጽዎ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርቧል።

የክልሉ ፖሊስ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ.ር) በክልሉ በየዓመቱ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የከተራ እና የጥምቀት በዓል ባማረና በደመቀ መልኩ በሰላም መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ለዚህ የጸጥታ ሥራ ስኬት የጸጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብር-ኃይል የመከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የክልሉ ፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት በመቀናጀት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በሙሉ ብቃት መወጣታቸውን ገልጸዋል።

ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ ሚናቸውን ለተወጡ የሃይማኖት አባቶች ትልቅ አክብሮት አለን ብለዋል።

በተለያዩ የክልሉ ከባቢዎች በዓሉ በሰላም እንዲከበር እና ለበዓሉ ድምቀት መላው የክልሉ ነዋሪዎች ላደረጉት አስተዋፅኦ እና ለተወጡት ኃላፊነት ምስጋና አቅርበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየበርግቢ ጋዲሎ ሜዳን የጥምቀት በዓል የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ ነው።