የከተራ እና ጥምቀት በዓላት በድምቀት ተከብረዋል።

28

 

ባሕር ዳር: ጥር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ውቤ የጥምቀት በዓል ስኬታማ በኾነ መንገድ እየተከበረ መኾኑን ተናግረዋል።

በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች ትናንት ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ወደ ጥምቀተ ባሕር ወርደዋል።

የከተራው በዓል በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በስኬት መከበሩን ተናግረው በጥምቀተ ባሕሩም የበዓሉ ሥነ ሥርዓት በስኬት ተካሂዷል ነው ያሉት።

ታቦታት ከጥምቀተ ባሕር ወደ ማዳሪያቸው ተመልሰዋል፤ ነገ ወደ መንበራቸው የሚመለሱ ታቦታት በመኖራቸው በዚያውም በጥምቀተ ባሕሩ የሚያድሩ አሉ፤ ሁሉም ሥነ ሥርዓት ስኬታማ በኾነ መንገድ እየቀጠለ ነው ብለዋል።

በዓሉ ስኬታማ እንዲኾን በቅንጅት መሠራቱን የተናገሩት ምክትል ኮሚሽነሩ የቅንጅት ሥራ በዓሉን ስኬታማ አድርጎታል ነው ያሉት።

በዓሉ ስኬታማ እንዲኾን የሃይማኖት አባቶች እና ወጣቶች የተጫወቱት ሚና ትልቅ መኾኑንም ተናግረዋል። እርሳቸው በተገኙበት በጎንደር ከተማ የጥምቀት በዓልን በስኬት ለማክበር ማኀበራት ከጸጥታ ተቋሙ ጋር መሥራታቸውን እና እየሠሩ መኾናቸውንም አስታውቀዋል።

ወጣቶች እና ማኅበራት ከከተራ ጀምሮ በዓሉ በሰላም፣ በፍቅር እና በደስታ እንዲከበር ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ መኾናቸውንም ገልጸዋል።

በከተራ እና በጥምቀት የታየው ውጤታማ ሥራ በቃና ዘገሊላ እና በሌሎች ሃይማኖታዊ በዓላት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ጥምቀትን ለማክበር በጎንደር እና በሌሎች ከተሞች ገብተዋል ያሉት ምክትል ኮሚሽነር አበበ ቆይታቸው ያማረ እንዲኾን በትኩረት እንሠራለን ነው ያሉት።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleጥምቀት የቱሪስት መዳረሻ እንዲኾን ከተማ አሥተዳደሩ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል።
Next articleየበርግቢ ጋዲሎ ሜዳን የጥምቀት በዓል የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ ነው።