“ክርስቶስ የተጠመቀው ከኃጥያት እንድንነጻ ነው”

7
አዲስ አበባ: ጥር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጥምቀት በዓልን በአዲስ አበባ በድምቀት አክብራለች።
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስን በመወከል መልዕክት ያስተላለፉት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አባ ጴጥሮስ በርጋ ክርስቶስ የተጠመቀው ካለንበት የኃጥያት መስመር ወጥትን እንድንነጻ ነው ብለዋል።
ጌታ በትህትና ወደ እኛ መጥቶ እሱ በንጽሕና ሳለ በኃጥያተኞች ስፍራ ቆሞ መጠመቁ እኛ በንስሐ እንድንመለስ ለማስተማር ነው ብለዋል።
ዛሬ “ምዕመናን በቅዱስ ውኃ ሲባረኩ እና ሲጠመቁ ከክርስቶስ ጋር ያላቸውን ዝምድና የሚያጠብቁበት እንደኾነ ነው” የገለጹት።
ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ክርስቶስ በዮርዳኖስ የተጠመቀው የጠፋውን የሰው ልጅ ለመፈለግ ነው” ብጹዕ አቡነ ሰላማ
Next articleጨለማ ወደ ብርሃን ይቀየር ዘንድ በጸሎት መትጋት ያስፈልጋል።