ዓለም ሊያየው የሚጓጓለት የጎንደር ጥምቀት በቅዱስ ፋሲለደስ ጥምቀተ ባሕር በተለያዩ ሥርዓቶች እየተከናወነ ነው። 

3

ባሕር ዳር፡ ጥር 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ሀገር ጎብኝዎች በታሪካዊው የቅዱስ ፋሲለደስ ጥምቀተ ባሕር የሚከወነውን አስደናቂ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓትን ለመመልከት ተገኝተዋል።

 

በዚህ ሰዓትም የቅዳሴ ሥርዓቱ እየተከናወነ ነው። በመቀጠልም ጥምቀተ ባሕሩ ከተባረከ በኃላ ሥርዓቱ በሚፈቅደው መልኩ ምዕመናን መጠመቅ ይጀምራሉ።

 

ወጣቶች ከርቀት እየዘለሉ ወደ ባሕሩ በመግባት የሚያሳዩት ድንቅ ትዕይንትም የሚቀጥል ይኾናል።

 

ጥምቀት በጎንደር የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ጎብኝዎችን የሚስብ ታላቅ በዓል ነው።

 

ንጉሠ ነገሥት አጼ ፋሲል ያሠሩት ባሕረ ጥምቀት ከጎንደር አልፎ ለመላው ኢትዮጵያ ምልክት እና የጎብኝ መዳረሻ ነው። ይህ በድንቅ ጥበብ እና አስተውሎት የተሠራው ጥምቀተ ባሕር የቀደመውን ታሪክ የሚገልጽ፣ ያማረ ሃይማኖታዊ ሥርዓት የሚፈጸምበት ታላቅ ሥፍራ ነው።

 

በክብረ በዓሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

 

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article‘’ጥምቀት ኢትዮጵያን የማሳያ ሙዚየም ነው’’ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው
Next articleየጥምቀት በዓል ጸሎተ ቡራኬ በባሕር ዳር