
ባሕር ዳር: ጥር 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለከተራ እና የጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ በመልካም ምኞት መልዕክታቸው የጥምቀት በዓል ለዓለም ያበረከትነው የሀገር እና የሕዝብ ሐብት እና ቅርስ ነው። የጋራ መገለጫ እሴትም ነው ብለዋል።
ጥምቀት ትህትና ርህራሄ የታየበት፣ ፀጋና በረከት የሚገኝበት፣ የደህንነትና የመለወጥ ተምሳሌት ነው።
በዓሉ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ እሴቶች የሚጎለብቱበት፣ ማሕበራዊ ግንኙነቶች የሚጠናከሩበት የአብሮነትና የአንድነት መድረክ ነው፡፡
ከሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ ይዘቱ በተጨማሪ ከፍ ያለ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አለው።
በዓሉ ማሕበራዊ እሴቶቻችን እንዲጠናከሩ፣ የሀገራችን መልካም ገጽታ ለዓለም ዓቀፉ ማሕበረሰብ ለማስተዋወቅ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
እነዚህ ኃይማኖታዊና ባሕላዊ ትውፊት እና እሴቶችን ጠብቀን በመያዝና በማዳበር ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ መስራት ይኖርብናል።
የጥምቀት በዓል የማዳን ጥበብ የታወጀበት፤ ደስታና ተስፋ የተገለጠበት በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ሰላምና ፍቅርን፤ አብሮነትና አንድነትን ለዓለም በማሳየት ሊሆን ይገባል።
ለእምነቱ ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የሰላም፣ የደስታና የአንድነት እንዲሆን እመኛለሁ።
መልካም የጥምቀት በዓል!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
