
ባሕር ዳር: ጥር 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ በተለምዶ ዓባይ ማዶ በሚባለው አካባቢ የሚገኙ ታቦታት በዓባይ ዳር ወደ ሚገኘው ጥምቀተ ባሕር እየወረዱ ነው።
በጥምቀተ ባህሩ አስራ ሰባት ታቦታት ይወርዳሉ። የየአብያተ ክርስቲያናቱ የሰንበት ተማሪዎች ያሬዳዊ ዝማሬ እየዘመሩ፣ በገና ደርዳሪዎች በበገና ምስጋና እያቀረቡ፣ ቀሳውስት እያመሰገኑ፣ ወጣቶችም በኾታ እያጀቡ ታቦታት ወደ ማደሪያቸው እያቀኑ ነው።
ዘጋቢ ፦ ፍሬሕይወት አዘዘው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
