
ከጥር እስከ ጥር ታሪክ፣ ባህል ትውፊትና እምነት ከሚነገርባት እና ከሚዘመርባት ሙዝየሟ ከተማ ጎንደር ገብተናል፡፡
ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ጋር በመኾን ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ስንደርስ የሞቀ አቀባበል ላደረጉልን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ የጎንደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ እንዲሁም ሌሎች የክልሉ አመራሮች እና የጎንደር ከተማ ታላላቆች ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ።
በከተማዋ በሚኖረን ቆይታ፣ ታሪካዊ ሥፍራዎችን እና ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን እንጎበኛለን፡፡
